የእናርጅ እናውጋ ወረዳ

የእናርጅ እናውጋ ወረዳ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙት ወረዳዎች መካከል አንዱ ሲሆን በሰሜን ጎንቻ ሲሶ እነሴ እና እነብሴ ሳር ምድር፣ በደቡብ እነማይና ሸበል በረንታ፣ በምዕራፍ እነማይ ደበይ ጥላት ግንና ሁለት ዕጁ እነሴ ወረዳዎች፣ በምስራቅ የአባይ ወንዝና የደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን ያዋስኑታል፡፡ ወረዳው ከደብረ ማርቆስ በ116 ኪ.ሜ. ርቀት በሰሜን ምሥራቅ ከክልሉ ዋና ከተማ ባ/ዳር ደግሞ በ187 ኪ.ሜ. በደቡብ ምሥራቅ እንዲሁም ከአ/አበባ በስተ ሰሜን በሞጣ ባህርዳር ዋና መስመር ላይ በ292 ኪ.ሜ.ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወረዳችን የውሃ ማማ ተብሎ የሚታወቀውን የጮቄ ተፋሰስንም ታቅፋ ትገኛለች፡፡ የወረዳው የቆዳ ስፋት 96,095.25 ሄ/ር /960.36 ካ.ኪሜ/ሲሆን ከዚህ ውስጥ 44,028 ሄ/ር ለእርሻ መሬት 2,316 ሄ/ር ለግጦሽ ፣3,278 ሄ/ር ለመንደርና ግባታዎች ፣2,630 ሄ/ር በቁጥቋጦና በጥሻ፣8,502 ሄ/ር ለደን የዋለ ፣145 ሄ/ር በቋሚ ተክል የተሸፈነ ሲሆን 35,196.25 ሄ/ር ደግሞ ለምንም አገልግሎት ሊውል የማይችል መሬት እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ከባህር ወለል በላይ ያለው ከፍታ ከ1,100—3,200 ሜትር በላይ ነው፡፡ የወረዳው የመሬት አቀማመጥ፡- ሜዳማ 50%፣ ተራራማ 30%፣ ሸለቋማ 20% ሲሆን የወረዳው የአየር ንብረት ፡- ቆላ 20%፣ ደጋ 30%፣ ወይና ደጋ 50% መሆኑን መረጃወች ያመለክታሉ፡፡ በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ውስጥ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ መስህቦች ይገኛሉ፡፡ ወረዳው የጥራጥሬ፣ የብእር እና የአገዳ፣ የስራስር እና የፍራፍሬ ሰብሎች የሚመረቱበት ለሰብል ምርት ተስማሚ የሆነ የአየር ጸባይ ካላቸው ወረዳወች መካከል አንዱ ነው፡፡ የእናርጅ እናውጋ ወረዳ የህዝብ ብዛት በገጠር ወንድ 84 384 ሴት 88 037ድምር 172 421 በከተማ ወንድ 19 813 ሴት 22 632 ድምር 42 445 በአጠቃላይ 214866 እንደሆነ ጥናት ያመላክታል፡፡ የወረዳው ርእሰ ከተማም ደብረ ወርቅ ናት፡፡





ኢንቨስትመንት

የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማጎልበት አስተዳደሩ ለባለሐብቱ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ባለሐብቱን በምደባ እና በጫራታ እየለየ ወደስራ እያስገባ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ጊዜም መሬት ለባለሐብቶች G+1 እስከ G+12 ደረስ ለተለያዩ አገልግሎቶች በመስጠት ወደስራ እየገቡ ይገኛሉ፡፡





የማዕድን ሃብታችን

ለኢንዱስትሪዎች ጥሬ እቃ የሚገልጸው የማዕድን ሃብታችን በተመለከተ በሁልም ቀበሌዎች ለኮንስትራክሽን ስራ አገልግሎት የሚውል ባለማዕዝን ድንጋይ ገረጋንቲ ያለ ቢሆንም በወረዳች አንዳንድ ቀበሌዎች ደግሞ የብረት ማዕድን ቀይ አሽዋ ፣ኖራ በአራራ እና ሶማ ቀበሌዎች ቢገኙም በመንገድ ችግር ምክንያት የልማቱ ተቋዳሽ አልሆኑም ፡፡ በ2012የበጀትዘመን8ባላሀብቶችኢንቨስትሊያደርጉፕሮጀክት ያቀርቡ ሲሆን በማነኛው ዘርፍ ለመስራት የሚፈልግ ኢንቨስተሪ 7ሄ/ር መሬት ተዘጋጅቶ በበመጠባበቅ ላይ ይገኛል ፣፣ ወረዳዋ ከ28በላይ ተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የመስህብ ሀብቶች ብሎም መልካም ምድራዊ አቀማመጥ የታደለች ከመሆኗም በላይ በርካታ ታሪካዊ ቦታዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተነስተው የሚፈሱ ወንዞች ባለቤት ናት፡፡ ከነዚህም መካከል አያልፉሽ፣ ፈላሴና የሶማ በርሃ ታሪካዊ ሰንሰለታማ ተራራዎች፤ በ15ኛው ክ/ዘ የተገነባው የፀሐይ ነገዳ ፍርስራሽ ግንብ፤ በ17ኛው ክ/ዘ የተገነባው የደጅ አዝማች ዩሐንስ ፍርስራሽ ግንብ፤ በታሪካዊነቷ የምትታወቀው የጥንታዊቷ የ1650 ዘመን ርዕሰ አድባር ደ/ወርቅ ማርያም ገዳም ና የታላቁ የጀር ቅ/ገብርኤል አንድነት ገዳም የሚገኙባት ናት፡፡ ነገር ግን ከቱሪዝም ፍሰት አኳያ ወረዳዋ ተጠቃሚ እየሆነች አይደለም ፡፡





ግብርና

መንግስት ግብርና መር ኢንዱስትሪልማትን ሰትራቴጂን በማሻሻል የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ወረዳዋ ለሰብል የተመቸ የአፈር አይነት እና የአየር ንብረት ያላት ወረዳ ብዙ አይነት ሰብሎችን ታበቅላለች፡፡ ከእነዚህ መካከል ጤፍ፣ ስንዴ፣ ባቄላ እና አተር ዋነኛዎቹ ሰብሎች ሲሆን ገበያ መር የሆነውን ቦለቄም በቆላማ ቀበሌዎች ታበቅላለች፡፡ አርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን አዳዲስ አሰራሮችን እንዲጠቀም በርካታ ስልጠናዎችን ተሠጥቶ ወደ ስራ በመግበቱ ምርታማነቱ ከ31.6ኩ/ል ወደ 39ኩ/ልበሄከታር በአማካኝ በማምረት ተጠቃሚ እየሆነ መጥቷል፡፡ በዚህም የራሱን ኑሮና ህወቱን ከመለወጥ ባለፈ እንደ ሃገርም በርካታ አስተዋጽኦ ማበርከት ተችሏል፡፡





ጤና

በወረዳችን ሚገኘውን ህዝብ የጤና ተጠቃሚ ለማድረግ ከከተማ እስከ ገጠር ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ፡፡ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮችን ከመፍጠር ጀምሮ ልዩልዩ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል 27 ጤና ኬላዎች ፣ 7 ጤና ጣቢያዎች 7 የግል ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም1 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያሉ ሲሆን የና ሽፋን 80% ማድረስ ተችሏል፡፡





ትምህርት

በዘመናዊ ትምህርት ቤትም 60 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፣ 4 ሁለተኛ ደረጃ ፣ 1 መሰናዶ ትምህርት ቤት እንዲሁም 1 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ይገኛል፡፡ በዚሁ በጀት ዓመት ብቻ በሁሉም የትምህርት ተቋማት ከ47 ሺ በላይ ተማሪዎች በመማር ላይ ይገኛሉ፡፡ ከትምህርት አንጻር ሃገራችን ከድህነት አራነቋ ለመለቀቅ የተማረ ዜጋ ወሳኝ መሆኑን ለመገንዘብ በርካታ ስራዎች ሲሰራ የቆየ ሲሆን እንደ ወረዳ የትምህርት ሽፋንን ለማዳረስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ61 በላይ 42 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣አንድ መሰናዶ ትመህርት ቤት ፣እንዲሁም 1 ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮለጅ የሚገኙባት ወረዳ ስትሆን 47 ሽህ በላይ ተማሪዎችን በመቀበል የመማር የማስተማርን ሂደት ተከናውናለች ፡፡ በአጠቃላይ ወረዳችን በርካታ ጸጋዎችና ምቹ ሁኔታዎች ያሏት ሲሆን በቱሪዝም ፣በማድን ፣በግብርና ዘርፍ እንዲሁም በሰው ሃብት ልማት የታደለች ከሞሆኑ ጋር ተየይዞ በላሃብቱ መጥቶ ቢያለማ ተጠቃሚየሚሆንበት እድል ሰፊ ነው፡፡





ኑ እናርጅን በጋራ እናልማ!